ማዕድናት
የማዕድናት ዓይነቶች እና ጠቀሜታ በኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በርካታ የማዕድን ዓይነቶች አሏት፡፡ ወርቅ ከከበሩ ማዕድናት አንዱ ነው፡፡ በጣም በሚስብ ቀለም፣ ዝገትን የመቋቋም እና በብዙ ልዩ ባህሪዎቹ ምክንያት በሰዎች ዘንድ በጣም የተከበረ ነው፡፡ ከፍተኛ የሆነ የወርቅ ክምችት በብዛት የሚገኘው በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉልና በሌሎች አካባቢዎች ነው፡፡
ኦፓል ብርሃንን የመሳብና የማንፀባረቅ ባህሪው የሰውን ዓይን መማረክ ብቻ ሳይሆን ቀልብንም በመሳብ የመጫጫን ስሜትን አስወግዶ ዘና የማለት ስሜትንና ውስጣዊ ሃይልን የሚያበረታታ ልዩ ማዕድን ነው፡፡
አኳማሪን ሌላው የከበረ ማዕድን ነው፡፡ እጅግ ከፍተኛ የሆነ መግነጢሳዊ ባህሪ ያለው ነው፡፡ ፈጣን ምላሽ የመስጠት ችሎታን ያጠናክራል፡፡
አሜቲስት በዓለም ላይ በጣም ተወዳጅ የሆነ ሐምራዊ ዕንቁ ነው ፡፡ አሜቲስት ዶቃዎችን እና ሌሎችን ጌጣጌጦች ለመስራት እና ለጌጣጌጥ አገልግሎት የሚውል ማዕድን ነው፡፡
የድንጋይ ከሰልም ሌላው የከበረ ማዕድን ሲሆን ከፍተኛ መጠን ያለው ካርቦን እና ሃይድሮካርቦኖች ያሉት ተቀጣጣይ ጥቁር ወይም ቡናማ ጥቁር የደለል ድንጋይ ነው። የድንጋይ ከሰል ለኃይል ምንጭነት ያገለግላል፡፡ የድንጋይ ከሰል ከሃይል ምንጭነት በተጨማሪ ለሲሚንቶ፣ ለብረታብረት እና ለጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ግብዓትነት ያገልግላል፡፡
ኳርትዝ የተሰኘውም ሌላኛው የከበረ ማዕድን ነው፡፡ ኳርትዝ በምድር ገጽ ላይ በሁሉም የአለም ክፍሎች የሚገኝ እና የተትረፈረፈ ነው፡፡ ኳርትዝ የብርጭቆ ወረቀት ብርጭቆ፣ የኮምፒውተር ዕቃዎችና ጌጣጌጥ ለመስሪያነት ይጠቅማል፡፡
ሩቢ በጣም ታዋቂ ከሆኑ የከበሩ ማዕድናት ተጠቃሹ ሲሆን ጌጣጌጥ ለመስራት በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ሩቢ የእጅ አምባር፣ የአንገት ጌጥ፣ ቀለበት እና የጆሮ ጌጥ ሌሎችንም የጌጣጌጥ ዓይነቶች ለመስራት ይጠቅማል፡፡ በሌሎች ጌጣጌጦች ላይ ፈርጥ በመሆን በርካታ ጌጣጌጦችን ለመስራት ይጠቅማል፡፡
ሳፋየር በዓለም ላይ ውድ ከሚባሉት ጌጣጌጦች ውስጥ የሚመደብ ሲሆን፣ ከአልማዝ በመቀጠል
ሁለተኛው ውድ ድንጋይ ነው። ብዙውን ጊዜ በቀን ብርሃን ሳፋየር የጥንካሬ ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ሰንፔር በተለያዩ ሀገራት በሀይማኖታዊና በባህላዊ መንገዶች እንደየቀለማቸው ሊያስገኙ ይችላሉ የሚባሉ ጥቅሞች አሉት። ሰማያዊ ሰንፔር በዓለም ላይ ሰንፔርን በቀለሙ ሰማያዊ ብቻ እንዲመስለን ያደረገ ተፅዕኖ ፈጣሪ ድንጋይ ነው። ቢጫ ሰንፔር በተለይ ለምግብ እንሽርሽሪትና የሆድን የውስጥ ሰላም ያመጣል ተብሎ ይታመናል። ለአዕምሯችን ትኩረትን ይጨምራል።
ኢመራልድ ሌላው የከበረ ማዕድን ሲሆን፣ ፕላቲኒየምን በመተካት ለቤተ-ሙከራ መሳሪያዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ለኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ለሞባይ ስልክ፣ ለዲቪዲ ማጫወቻና ለኮምፒዩተሮች ይጠቅማል፡፡ (more…)
