የባህል ትስስር ትርጉም
- የባህል ትስስር በአንፃራዊነት አዲስ መደበኛ የሆነ የማህበራዊ ሳይንስ ጥናት መስክ ነው።
- ከሌሎች ጋር በተለይም የተለያየ ባህል ካላቸው ጋር የመስማማት ችሎታን ይመለከታል።
- ግላዊ እና ማህበራዊ ግንኙነቶችን መጀመር እና ማቆየት የሰው ልጅ አስፈላጊ የህይወት ክፍል ነው፡፡
- የሰዎች ግንኙነት በማህበራዊ ፍላጎቶች ላይ ተመስርቶ ከሌሎች ጋር የማገናኘት መስተጋብር ሂደት ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡
- ሰዎች በማህበራዊ ቡድኖች፣በቤተሰብ፣ በጓደኝነት፣ በጎሳ በመሳሰሉት በመደራጀት እርስ በእርስ የተሳሰሩ ናቸዉ፡፡
- የባህል ትስስር ጥናት በማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዉስጥ ሰዎች ከራሳቸው ባህል ውጭ እንዲረዱ፣ እንዲግባቡ እና የተወሰኑ ግቦችን እንዲያሳኩ ለማሰልጠን የተነደፈ ተግባራዊና ባለብዙ መስክ ጥናት ነው።
- የባህላዊ ግንኙነቶች በመሠረታዊ ደረጃ ራስን እና ዓለምን በሌላ ዓይን እንዴት ማየት እንደሚችሉ መማርን ያካትታል።
- ዛሬ ላይ ዓለማችን በመገናኛ ብዙኃን፣ ኢንተርኔት እና ቴክኖሎጂ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ላይ በሚያሳድሩት ተጽዕኖ ምክንያት ብሔራዊ ድንበሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደበዘዙ በመምጣት ዓለም ወደ ሉላዊነት ተለዉጣለች።
