ምዕራፍ አንድ -የከተማችን መገኛ
ተማሪዎች! በሶስተኛ ክፍል በአዲስ አበባ ስለሚገኙ ክፍለ ከተሞች መገኛ፣ስለ አንጻራዊና ፍፁማዊ መገኛ ምንነትና በክፍለ ከተማችሁ ስለሚገኙ ዋናዋና ቦታዎች ተምራችኋል፡፡ በአራተኛ ክፍል ደግሞ ስለ ከተማችሁ መገኛ፣ስለ ካርታ ምንነት፣ ስለ አንጻራዊና ፍጹማዊ መገኛ ምንነት፣ ስለ ከተማችሁ አንፃራዊና ፍጹማዊ መገኛ፣በከተማችሁ ስለሚገኙ ዋና ዋና ቦታዎች መገኛ፣ርቀት፣አቅጣጫና አዋሳኝ ክልሎች መገኛ በዝርዝር ትማራላችሁ፡፡
ምዕራፍ ሁለት -ሳይንስን መገንዘብ
በሦሥተኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ ትምህርት ሳይንስን መገንዘብ በሚል ምዕራፍ ውስጥ ስለምን እንደተማራችሁ ታስታውሳላችሁ? ስለጤናማ ምግቦችና መጠጦች
መለየት፣ አራቱን ዋና ዋና የምግብ ምድቦች፣ የምግብ ብክለት መከላከያ ዘዴዎችና
የንፅህና መጠበቂ ዘዴዎችን ተምራችኋል፡፡ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ደግሞ ስለ
ምግብና ጤናማ አኗኗር፣ አልሚ ምግቦች፣ የተመጣጠነ ምግብ፣ የቁስ አካላት
ባህርያትንና የጥላ አፈጣጠርን በዝርዝር ትማራላችሁ::
ምዕራፍ ሦስት -ተፈጥሮአዊ አካባቢ
ተፈጥሮአዊ አካባቢያችን ለኑሮ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ይሰጠናል፡፡ በዚህ ክፈለ
ትምህርት ስለተፈጥሮ ሀብቶች እና እንክብካቤአቸው ትማራላችሁ፡፡ተማሪዎች በሦስትኛ ክፍል ትምህርታችሁ በክፍለ ከተማችሁ ስላለው የአየር ንብረት ሁኔታ፣ የአየር ንብረት ይዘቶችና ተቆጣጣሪዎች እንዲሁም በክፍለ ከተማችሁ ስለሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች፣ ስለ ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና እንክብካቤ ዘዴዎችና ስለ ቆሻሻ አወጋገድ ሁኔታዎች ተምራችኋል፡፡በዚህ ምዕራፍ ደግሞ በከተማችሁ አዲስ አበባ ስላለው የአየር ንብረት ሁኔታ፣የአየር ንብረት ይዘቶችና ተቆጣጣሪዎች እንዲሁም በክፍለ ከተማችሁ ስለሚገኙየተፈጥሮ ሀብቶች፣ ስለ ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና እንክብካቤ ዘዴዎችና ስለ ቆሻሻአወጋገድ ሁኔታዎች ትማራላችሁ፡፡
ምዕራፍ አራት -ማህበራዊ አካባቢ
ተማሪዎች! በሦስተኛ ክፍል የአካባቢ ሳይንስ ትምህርት ስለባህል ምንነትና ትርጉም
ተምራችኋል፡፡በዚህ ምዕራፍ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙትን ባህሎች፣ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ አስተዋፆኦ ያላቸውን ባህላዊ አሰራሮች፣ለባህሎች
ብዝሃነት ዋጋ መስጠትን፣የከተማችን ምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴዎችን፣በከተማችን
ለገበያ ሊውሉ የሚችሉ የተፈጥሮ ሀብቶችና ውጤቶችን፣በተፈጥሮ ሀብትና
ውጤቶች ላይ የሚደረግ ሕጋዊና ሕገወጥ የንግድ ክዋኔዎችን፣በከተማችን የሚገኙ ለሰዎችና ለዕቃዎች የሚያገለግሉ የተለያዩ የመጓጓዣ ዘዴዎችንና በከተማችን
የሚገኙ ቅርሶችን በዝርዝር ትማራላችሁ፡፡
ምዕራፍ አምስት -ምዕራፍ አምስት
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች መካከል ዋና ዋናዎቹን ትማራላችሁ፡፡ የመረጃ ቴክኖሎጅን በመጠቀም የኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ ስርጭት እና የሚያስከትለዉን ጉዳት እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ትገልፃላችሁ፡፡ የአደገኛ ኬሚካሎችን እና አደንዛዥ እፆችን ምንነት ትለያላችሁ::እንዲሁም ተገቢነት የሌለው መድኃኒት አጠቃቀምን ምንነትና በሰዎች ጤናላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ትገነዘባላችሁ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ስለ ድርቅ ና ረሃብ ምንነት ፣ የድርቅ ምክንያትና ውጤት ትገነዘባላችሁ፡፡ በስተመጨረሻም የከተማችሁን የዝናብ መጠን የሚያሳይ ካርታ በመመልከት ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን እና በከተማችሁ ድርቅን ለመቋቋም የሚያስችሉ ዘዴዎችንትለያላችሁ፡፡
Course Features
- Lectures 7
- Quizzes 1
- Duration 35 weeks
- Skill level All levels
- Language አማርኛ
- Students 5
- Certificate No
- Assessments Self
Curriculum
- 6 Sections
- 7 Lessons
- 35 Weeks
- ምዕራፍ አንድ -የከተማችን መገኛ7
- ምዕራፍ ሁለት -ሳይንስን መገንዘብ0
- ምዕራፍ ሦስት -ተፈጥሮአዊ አካባቢ1
- ምዕራፍ አራት -ማህበራዊ አካባቢ0
- ምዕራፍ አምስት -ምዕራፍ አምስት0
- 6ኛ ሳምንት1







1 Comment
ሚስተር 2, ኛው ጥያቄ ታዳሽ የተፈጥሮ ብዬ
(×) ምልክት ሰቶኝ መልሱ ምንድነው ብዬ ሳይ
ታዳሽ የተፈጥሮ ሲል እኔ የፃፍኩት እና መልሱ
አንድ ሆኖ (×) አደረገኝ። መልስ እፈልጋለሁ
{ አመሰግናለሁ ሚስተር }
{ከሄሜን ተሾመ 4ሀ ክፍል}