ሰት በአዕምሯችን የሚመላለስን ጉዳይ በጽሑፍ የማስተላለፍ /የማንጸባረቅ/ ስልት ነው፡፡ በውስጡም ፈጠራዊ እና ፈጠራዊ ያልሆኑ ገዳዮች እየተነሱ ሊብራሩና ትንታኔ ሊቀርብባቸው ይችላል፡፡ አጠቃላይ ድርሰት ልቦለዳዊ ወይም ኢልቦለዳዊ ተብሎ በሁለት ይከፈላል፡፡ ልቦለዳዊ ድርሰት የምንለው ፈጠራዊ ሥራን የሚያመለክት ሲሆን በውስጡም ኪናዊ ለዛ ያላቸውን ሥነጽሑፋዊ ሥራዎች ያካትታል፡፡
ኢልቦለዳዊ ድርሰት ደግሞ እውነተኛ የሆኑ ኩነቶችን በጽሑፍ የምናስተላልፍበት መንገድ ነው፡፡ ከተከሰተው ኩነት ዘርፋዘርፍ ሳንጨምር ማለትም ሳንከልስና ሳንበርዝ እንዳለ ማቅረብ ነው፡፡
ድርሰት በምንጽፍበት ጊዜ የምንከተላቸው መርሆች
ድርሰት በምንጽፍበት ጊዜ ልንከተላቸው የሚገባን (ሊያግዙን የሚችሉ) መርሆች አሉ፡፡ እነርሱም ድርሰት ከመጻፋችን በፊት እንዲሁም በምንጽፍበት ጊዜ የምንከተላቸው ናቸው፡፡
፩. ድርሰት ከመጻፋችን በፊት (ቅድመ ድርሰት ተግባር) ቀጥለን የምንዘረዝራቸው ተግባራት ድርሰት ከመጻፋችን በፊት የምንፈጽማቸው ናቸው፡፡
1.1 ራሳችንን ድርሰት ለመጻፍ ማነሳሳት፡- በዚህ ተግባር ሥነ- ልቦናችሁን ዝግጁ የማድረግ ተግባር የሚፈጸምበት ነው፡፡
1.2 ድርሰት የመጻፍ ዓላማ፡- ድርሰት የመጻፍ ዓላማ የምንለው ለማን፣ ለምን እንዴት እጽፋለሁ የሚለውን ቀድመን መመለስ የሚገቡን ጥያቄዎች የምንመልስበት ተግባር ነው፡፡
1.3 ርዕስ መምረጥ፡- የሚመረጠው ርዕስ ሳቢ፣ ግልጽና አጭር መሆን አለበት፡፡
1.4 ርዕስ ማጥበብ/መወሰን/፡- የምንጽፈው ድርሰት ሊዳስስ የሚችላቸውን ነጥቦች የምንወስንበት ነው፡
1.5 አስተዋጽኦ /ቢጋር/ ማዘጋጀት፡- የምንጽፈው ድርሰት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ፍሰቱን ጠብቆ እንዲጻፍ የሚያግዘን ትልም ወይም መንገድ ቀያሽ ነው፡፡
1.6 መረጃ ማፈላለግ፡- በርዕሱ መሰረት ከሰዎች፣ ከመጻሕፍት ወይም ከመገናኛ ብዙሀን ልንፈልግ እንችላለን፡፡
1.7 መረጃዎችን መምረጥ/መለየት/፡- ከርዕሳችን ጋር የሚስማሙና ተመሳሳይነት ያላቸው ነጥቦች ብቻ የሚቀርቡበት ነው፡፡
1.8 የተደራሲ ዓውድ፡- የምንጽፈው ድርሰት በሰዎች ተቀባይነት እንዲያገኝ የምናደርግበት ነው፡፡፪. ድርሰት በምንጽፍበት ጊዜ (የጽሕፈት ተግባር)
2.1 ረቂቅ መጻፍ፡- በተነደፈው ቢጋር መሰረት መጀመሪያውን የመጣልን ሀሳብን ማስፈር ነው፡፡
2.2 አርትኦት /እደታ/፡- የፊደል፣ የቃል ወይም የዓረፍተ ነገር ግድፈት እንዳይኖር ሙሉ ጥንቃቄ ተደርጎ የሚታረምበት ነው፡፡
2.3 የመጨረሻ ረቂቅ መጻፍ፡- ፀሀፊው ማድረግ የሚገባውን ሁሉ መፈፀሙን ባመነ ጊዜ ተከታዩ ተግባር በተፃፈበት ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሙያ ያላቸው ሰዎች አንብበው ተገቢ ማስተካከያ፤ አስተያየትና ምዘና እንዲሰጡ ማድረግ ነው፡፡
Course Features
- Lectures 1
- Quizzes 0
- Duration 36 weeks
- Skill level All levels
- Language English
- Students 0
- Certificate No
- Assessments Yes
Curriculum
- 2 Sections
- 1 Lesson
- 36 Weeks
- ምዕራፍ 21
- ምዕራፍ 30




