ምዕራፍ አንድ – የክፍለ ከተማችን መገኛ
ተማሪዎች! በሁለተኛ ክፍል ስለወረዳ ምንነትና መገኛ ተምራችኋል። በሦስተኛ ክፍል ደግሞ ስለአንጻራዊ መገኛ ምንነት፣ ስለፍጹማዊ መገኛ ምንነት፣ ስለክፍለ ከተማችሁ አንጻራዊ መገኛ ፍጹማዊ መገኛ፣ በክፍለ ከተማችሁ ስለሚገኙ ዋና ዋና ቦታዎች መገኛ ስለክፍለ ከተማችሁ አዋሳኝ ክፍለ ከተሞች መገኛና ስማቸው ትማራላችሁ፡፡ ክፍለ ከተማ የተለያዩ ወረዳዎችን የያዘ የአስተዳደር እርከን ነው። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዐሥራ አንድ ክፍለ ከተሞች ይገኛሉ።
እነርሱም፡- ለሚ ኩራ፣ልደታ ፣ ቂርቆስ፣ ቦሌ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ አራዳ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ አዲስ ከተማ ፣ ኮልፌ ቀራንዮ ፣ የካ እና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ናቸው።
ምዕራፍ ሁለት – ሳይንስን መገንዘብ
ተማሪዎች! በሁለተኛ ክፍል ስለምግብ ጥቅሞች፣ ስለብርሃን ምንነት፣ስለ ብርሃን
ምንጮችና ስለ ቁስ አካል ባህሪያት ተምራችኋል፡፡ በሦስተኛ ክፍል ደግሞ ስለምግብና
ጤና ፣ ስለምግብ ጥቅም ፣ስለምግብ ብክለት መንስኤዎች ፣ ስለግል ንፅህና አጠባበቅ
፣ ስለቁስ አካላት ሁነቶች እና የብርሃን ጥቅሞች ትማራላችሁ።
ምግብ ሰውነትን ለመገንባት፣ የተጎዱ አካሎቻችንን ለመጠገን ፣ ከተለያዩ በሽታዎች
ለመከላከልና ጉልበት ለማግኘት ይጠቅመናል፡፡ የሰው ልጅ ጤንነቱን ለመጠበቅ
ማድረግ ከሚገባው ነገሮች አንዱ ምግብን በጥንቃቄ መያዝና መመገብ ነው። የግልና
የአካባቢያችንን ንፅሕና በመጠበቅ ራስን ከበሽታ መከላከል ይቻላል።
በትምህርቱም ሂደት እንደ መመልከት ፣ መጠየቅ ፣ ስዕላዊ መግለጫዎችን መተርጎም
መግባባትና ተባብሮ መሥራት የመሳሰሉትን የሳይንሳዊ ምርምር ክህሎቶችን
ታዳብራላችሁ።ስለሆነም ለትምህርታችሁ ትኩረት በመስጠት በንቃት እየተሳተፋችሁ
መማር ይጠበቅባችኃል፡፡
ምዕራፍ ሦስት -ተፈጥሮአዊ አካባቢ
የተፈጥሮ አከባቢያችን ሕይወት ያላቸውንና ሕይወት የሌላቸውን ነገሮች
ይይዛል፡፡ ሕይወት ያላቸው ነገሮች እፅዋትና እንሰሳት ናቸው፡፡ ሕይወት የሌላቸው ነገሮች
አየር፣ አፈር፣ ውሃ፣ ማዕድናትና የመሳሰሉት ናቸው። የሰው ልጅ ሕይወት ያላችውንና
ሕይወት የሌላቸውን ነገሮች መሠረታዊ ፍላጎቱን ለማሟላት ይጠቀምባቸዋል፡፡
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ስለ ክፍለ ከተማችሁ የአየር ሁኔታና የአየር ንብረት፣ የተፈጥሮ
እና ሰው ሠራሽ ሐብቶች፣ የተፈጥሮ ሐብቶች ለክፍለ ከተማችሁ ሕልውናና ዕድገት
ስላላቸው ፋይዳ ፣ በትምህርት ቤትና በወረዳችሁ የሚስተዋሉ ተገቢ እና ተገቢ
ያልሆኑ የቆሻሻ አወጋገድ ዘዴዎች እና ተገቢ ያልሆነ የቆሻሻ አወጋገድ ተፅዕኖዎች
ትማራላችሁ። ስለዚህ የተፈጥሮ ሐብቶችን በጥንቃቄና በብልሐት ጥቅም ላይ ማዋል
ይጠበቅብናል፡፡
ምዕራፍ አራት -ማኅበራዊ አካባቢ
ተማሪዎች! በሁለተኛ ክፍል የአካባቢ ሳይንስ ትምህርታችሁ ስለቤተሰብና ስለወረዳችሁ
ማኅበረሰብ ተምራችኋል። በዚህ ክፍል ደግሞ ስለክፍለ ከተማችሁ የባህል ብዝኀነት
ትማራላችሁ። ከዚህ በተጨማሪ በክፍለ ከተማችሁ ስላለው የምጣኔ ሀብታዊ
እንቅስቃሴዎች ትማራላችሁ።
ምዕራፉ ሲጠናቀቅ የሚጠበቅባችሁን ዕውቀትና ክህሎት እንድትቀስሙ ትምህርቱን
በንቃት መከታተል አለባችሁ።
ምዕራፍ አምስት -ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች
ተማሪዎች! በሁለተኛ ክፍል በምዕራፍ አምስት ትምህርታችሁ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ
ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች በሚል ርዕስ ስለትራፊክ ደንቦች እና ኤች.አይ.ቪ./ ኤድስ
ተምራችኋል። በሦስተኛ ክፍል ትምህርታችሁም ስለመንገድ ደኅንነትና
ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምልክቶችና በመድኃኒቶች መካከል ስላለው ግንኙነት ትማራላችሁ።
Course Features
- Lectures 3
- Quizzes 1
- Duration 35 weeks
- Skill level All levels
- Language አማርኛ
- Students 6
- Certificate No
- Assessments Self
Curriculum
- 5 Sections
- 3 Lessons
- 35 Weeks
- ምዕራፍ ሁለት - ሳይንስን መገንዘብ0
- ምዕራፍ ሦስት -ተፈጥሮአዊ አካባቢ0
- ምዕራፍ አራት -ማኅበራዊ አካባቢ1
- ምዕራፍ አምስት -ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች0
- 6ኛ ሳምንት4





5 Comments
በጣም ጥሩ ነው በምሳሌ እንደዚህ ሲቀርብ ለልጆችም ሆነ ለእኛ ለወላጆች በጣም ግልፅ ይሆናል፡፡በዚሁ ቀጥሉበት እናመሠግናለን፡፡
Were is Work sheet
ያንተ ክዊዠ አልተላከም
It is good
እስከ ምዕራፍ አምስት የነበረውን ኖት እዚህ ላይ መቀመጡ ጥሩ ቢሆንም አሁን ላይ እየተማሪ ስላሉት ማለትም ስለ ደም ….. ከመፅሃፋቸውም ላይ ማግኘት ስለማንችል ለማስጠናት ይረዳን ዘንድ በዚህ ገፅ ላይ አጠር ያለ ኖት ብትለቁልን መልካም ነው::